ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 61:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ጸሎቴንም አድምጥ።

2. ልቤ በዛለ ጊዜ፣ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።

3. አንተ መጠጊያዬ፣ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና።

4. በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤በክንፎችህም ጥላ ልከለል። ሴላ

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 61