ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 6:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህአትገሥጸኝ፤በመዓትህም አትቅጣኝ።

2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ።

3. ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤እስከ መቼ፤ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል?

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤

5. በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል?

6. ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ፤ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።

7. ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኖአቸዋል።

8. እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቶአልና።

9. እግዚአብሔር ልመናዬን አድምጦአል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 6