ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 58:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤አልሰማ ብላ ጆሮዋን እንደ ደፈነች እፉኝት ናቸው፤

5. ጆሮዋንም የደፈነችው የመተተኛውንወይም የጠቢቡን ደጋሚ ቃል ላለመስማት ነው።

6. አምላክ ሆይ፤ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንበሶቹን መንጋጋ አወላልቅ!

7. ፈጥኖ እንደሚያልፍ ወራጅ ውሃ ይጥፉ፤ቀስታቸውን ሲስቡ ፍላጻቸው ዱልዱም ይሁን።

8. ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ፀሓይን እንደማያይ ጭንጋፍ ይሁኑ።

9. የእሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሰማው፣እርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 58