ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 57:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ለእግሬ ወጥመድን ዘረጉ፤ነፍሴንም አጐበጧት፤በመተላለፊያዬ ላይ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት። ሴላ

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ልቤ ጽኑ ነው፤እቀኛለሁ፤ አዜማለሁ።

8. ነፍሴ ሆይ፤ ንቂ!በገናና መሰንቆም ተነሡእኔም በማለዳ እነሣለሁ።

9. ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ፤

10. ምሕረትህ እስከ ሰማያት ከፍ ብላለችና፤ታማኝነትህም እስከ ደመናት ትደርሳለች።

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትስፈን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 57