ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 56:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል።

2. ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና።

3. ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

4. ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

5. ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 56