ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 56:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል።

2. ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና።

3. ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

4. ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

5. ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።

6. ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቶ እንዳያመልጡ፣ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።

8. ሰቆቃዬን መዝግብ፤እንባዬን በዕቃህ አጠራቅም፤ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን?

9. ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።

10. ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ቃሉን በማመሰግነው በእግዚአብሔር፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 56