ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 52:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ?አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?

2. አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣ጥፋትን ያውጠነጥናል።

3. ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣እውነትን ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ወደድህ። ሴላ

4. አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፤ጐጂ ቃላትን ሁሉ ወደድህ!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 52