ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 51:5-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ስወለድ ጀምሮ በደለኛ፣ገና እናቴም ስትፀንሰኝ ኀጢአተኛ ነኝ።

6. እነሆ፤ እውነትን ከሰው ልብ ትሻለህ፤ስለዚህ ጥልቅ ጥበብን በውስጤ አስተምረኝ።

7. በሂሶጵ እርጨኝ፤ እኔም እነጻለሁ፤እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።

8. ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፤ያደቀቅሃቸው ዐጥንቶቼም ደስ ይበላቸው።

9. ፊትህን ከኀጢአቴ መልስ፤በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።

10. አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

11. ከፊትህ አትጣለኝ፤ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ።

12. የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 51