ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 51:11-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ከፊትህ አትጣለኝ፤ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ።

12. የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።

13. እኔም ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ፤ኀጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።

14. የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል።

15. ጌታ ሆይ ከንፈሮቼን ክፈት፤አፌም ምስጋናህን ያውጃል።

16. መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ ባቀረብሁልህ ነበር፤የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም።

17. እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤እግዚአብሔር ሆይ፤አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።

18. በበጎ ፈቃድህ ጽዮንን አበልጽጋት፤የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች ሥራ።

19. የጽድቅ መሥዋዕት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና፣ሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያን ጊዜ ደስ ያሰኙሃል፤ኮርማዎች በመሠዊያህ ላይ የሚሠዉትም ያን ጊዜ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 51