ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 50:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እኔ ግን ኮርማህን ከበረት፣ፍየሎችህንም ከጒረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤

10. የዱር አራዊት ሁሉ፣በሺ ተራራዎች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና።

11. በየተራራው ያለውን ወፍ ሁሉ ዐውቃለሁ፤በሜዳ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ የእኔ ነው።

12. ብራብ ለአንተ አልነግርህም፤ዓለምና በውስጧ ያለውም ሁሉ የእኔ ነውና።

13. ለመሆኑ፣ እኔ የኰርማ ሥጋ እበላለሁን?የፍየልንስ ደም እጠጣለሁን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 50