ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 50:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኀያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር ተናገረ፤ከፀሓይ መውጫ እስከ ፀሓይ መግቢያ ድረስ ምድርን ጠራት።

2. ፍጹም ውብ ከሆነችው ከጽዮን፣እግዚአብሔር አበራ።

3. አምላካችን ይመጣል፤ ዝምም አይልም፤የሚባላ እሳት በፊቱ፣የሚያስፈራ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው አለ።

4. በሕዝቡ ይፈርድ ዘንድ፣በላይ ያለውን ሰማይንና ምድርን እንዲህ ብሎ ይጠራል፤

5. “በመሥዋዕት ከእኔ ጋር ኪዳን የገቡትን፣ቅዱሳኔን ወደ እኔ ሰብስቧቸው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 50