ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 49:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ።

2. ዝቅተኞችና ከፍተኞች፤ባለጠጎችና ድኾች ይህን በአንድነት ስሙ።

3. አፌ የጥበብን ቃል ይናገራል፤የልቤም ሐሳብ ማስተዋልን ይሰጣል።

4. ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።

5. የአጭበርባሪዎች ክፋት በከበበኝ ጊዜ፣በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?

6. በሀብታቸው የሚመኩትን፣በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?

7. የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።

8. የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና፤በቂ ዋጋም ከቶ ሊገኝለት አይችልም፤

9. በዚህም ዘላለም ይኖራል፣መበስበስንም አያይም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 49