ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 48:5-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. አይተውም ተደነቁ፤ደንግጠውም ፈረጠጡ።

6. ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣በዚያ ብርክ ያዛቸው።

7. የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣አንተ አብረከረክሃቸው።

8. እንደ ሰማን፣በሰራዊት አምላክ ከተማ፣በአምላካችን ከተማ፣እንዲሁ አየን፤እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ

9. አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ምሕረትህን እናስባለን።

10. አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።

11. ስለ ፍርድህ፣የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።

12. በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤የጥበቃ ግንበኞቿንም ቍጠሩ፤

13. ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ።

14. ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 48