ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 48:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል።

2. የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው።

3. እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፤ብርቱ ምሽግ እንደሆናት አስመስክሮአል።

4. እነሆ፤ ነገሥታት ተባብረው መጡ፤አንድ ላይ ሆነውም ገሠገሡ።

5. አይተውም ተደነቁ፤ደንግጠውም ፈረጠጡ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 48