ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 46:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የእግዚአብሔርን ከተማ፣የልዑልን የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኝ የወንዝ ፈሳሾች አሉ።

5. እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤አምላክ በማለዳ ይረዳታል።

6. ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታትም ወደቁ፤ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።

7. የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ

8. ኑና የእግዚአብሔርን ሥራ፣ምድርንም እንዴት ባድማ እንዳደረጋት እዩ።

9. ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 46