ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 45:9-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።

10. ልጄ ሆይ፤ አድምጪ፤ አስተዉይ፤ ጆሮሽንም አዘንብይ፤ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።

11. ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል፤ጌታሽ ነውና አክብሪው።

12. የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።

13. የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው።

14. በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣ወደ አንተ ይመጣሉ።

15. በደስታና በሐሤት ወደ ውስጥ ይመሯቸዋል፤ወደ ንጉሡም ቤተ መንግሥት ይገባሉ።

16. ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ፤ገዦችም አድርገሽ በምድር ሁሉ ትሾሚያቸዋለሽ።

17. ስምሽን በትውልድ ሁሉ ዘንድ መታሰቢያ አደርጋለሁ፤ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ያወድሱሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 45