ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 45:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል።

9. ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።

10. ልጄ ሆይ፤ አድምጪ፤ አስተዉይ፤ ጆሮሽንም አዘንብይ፤ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።

11. ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል፤ጌታሽ ነውና አክብሪው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 45