ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 45:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል፤ጌታሽ ነውና አክብሪው።

12. የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።

13. የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው።

14. በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣ወደ አንተ ይመጣሉ።

15. በደስታና በሐሤት ወደ ውስጥ ይመሯቸዋል፤ወደ ንጉሡም ቤተ መንግሥት ይገባሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 45