ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 44:6-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በቀስቴ አልተማመንም፤ሰይፌም አያስጥለኝም።

7. አንተ ግን በጠላቶቻችን ላይ ድልን ትሰጠናለህ፤ባላንጣዎቻችንንም ታሳፍራለህ።

8. ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን፤ስምህንም ለዘላለም እንወድሳለን። ሴላ

9. አሁን ግን እነሆ ትተኸናል፤ አሳፍረኸናልም፤ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም።

10. ከጠላት ፊት እንድናፈገፍግ አደረግኸን፤ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን።

11. እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤በሕዝቦችም መካከል በተንኸን።

12. ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።

13. ለጎረቤቶቻችን ስድብ፣በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 44