ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 44:15-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ውርደቴ ቀኑን ሙሉ በፊቴ ነው፤ፊቴም ዕፍረትን ተከናንቦአል።

16. ይህም ከሚዘልፍና ከሚያላግጥ ሰው ድምፅ የተነሣ፣ከጠላትና ከተበቃይ ሁኔታ የተነሣ ነው።

17. አንተን ሳንረሳ፣ለኪዳንህም ታማኝነታችንን ሳናጓድል፣ይህ ሁሉ ደረሰብን።

18. ልባችን ወደ ኋላ አላለም፤እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም።

19. አንተ ግን ተኵላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤በሞት ጥላም ሸፈንኸን።

20. የአምላካችንን ስም ረስተን፣እጃችንንም ወደ ባዕድ አምላክ ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣

21. እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሳነዋልን?እርሱ ልብ የሰወረውን የሚረዳ ነውና።

22. ይሁን እንጂ ቀኑን ሙሉ ስለ አንተ ሞትን እንጋፈጣለን፤እንደሚታረዱ በጎችም ተቈጥረናል።

23. ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ?ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።

24. ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?መከራችንንና መጠቃታችንን ለምን ትረሳለህ?

25. ነፍሳችን ዐፈር ውስጥ ሰጥማለች፤ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቆአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 44