ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 43:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፤ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።

2. አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣ለምን ተውኸኝ?ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?

3. ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤እነርሱ ይምሩኝ፤ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።

4. እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣በበገና አመሰግንሃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 43