ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 41:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።

10. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ።

11. ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣እንደ ወደድኸኝ በዚህ አወቅሁ።

12. ስለ ጭንቀቴ ደግፈህ ይዘኸኛል፤በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።

13. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ ይሁን፤አሜን፤ አሜን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 41