ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 41:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለድኾች የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው፤እርሱንም እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል።

2. እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ለጠላቶቹም ምኞትም አሳልፎ አይሰጠውም።

3. ታሞ ባለበት ዐልጋ ላይ እግዚአብሔር ይንከባከበዋል፤በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል።

4. እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረት አድርግልኝ፤አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ።

5. ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስየሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ።

6. ሊጠይቀኝ የሚመጣ ቢኖር፣በልቡ ስድብ እያጠራቀመ፣ ከዐንገት በላይ ይናገራል፤ወጥቶም ወሬ ይነዛል።

7. ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤እንዲህ እያሉም፣የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤

8. “ክፉ ደዌ ይዞታል፤ከእንግዲህም ከተኛበት አይነሣም።”

9. እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ።

10. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ።

11. ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣እንደ ወደድኸኝ በዚህ አወቅሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 41