ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 40:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ።

2. ከሚውጥ ጒድጓድ፣ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤አካሄዴንም አጸና።

3. ለአምላካችን የሚሆን ውዳሴ፣አዲስ ዝማሬን በአፌ ላይ አኖረ፤ብዙዎች ያያሉ፤ ይፈራሉም፤ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።

4. እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ፣ሰው ብፁዕ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 40