ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 4:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የጽድቄ አምላክ ሆይ፤በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።

2. ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅ ታደርጋላችሁ?እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስ ትሻላችሁ? ሴላ

3. እግዚአብሔር ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።

4. ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ

5. የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤ በእግዚአብሔርም ታመኑ።

6. ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል? ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 4