ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 38:17-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ልወድቅ ተቃርቤአለሁ፤ከሥቃዬም ከቶ አልተላቀቅሁም።

18. በደሌን እናዘዛለሁ፤ኀጢአቴም አውካኛለች።

19. ብርቱዎች ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤ያለ ምክንያት የሚጠሉኝም ስፍር ቊጥር የላቸውም።

20. መልካሙን ስለ ተከተልሁ፣በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ ጠሉኝ።

21. እግዚአብሔር ሆይ፤ አትተወኝ፤አምላኬ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።

22. ጌታዬ መድኅኔ ሆይ፤እኔን ለመርዳት ፍጠን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 38