ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 38:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ከቊስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ።

12. ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ።

13. እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቈሮ፣አፉንም መክፈት እንደማይችል ዲዳ ሆንሁ።

14. በእርግጥም ጆሮው እንደማይሰማ፣አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ።

15. እግዚአብሔር ሆይ፤ በተስፋ እጠብቅሃለሁ፤ጌታ አምላኬ ሆይ፤ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 38