ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 37:35-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

35. ክፉና ጨካኙን ሰው፣እንደ ሊባኖስ ዝግባ ለምልሞ አየሁት፤

36. ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤ብፈልገውም አልተገኘም።

37. ንጹሐንን ልብ በል፤ ቅኑንም አስተውል፤የሰላም ሰው ተስፋ አለውና።

38. ኀጢአተኞች ግን በአንድነት ይጠፋሉ፤የክፉዎችም ዘር ይወገዳል።

39. የጻድቃን ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤በመከራ ጊዜም መጠጊያቸው እርሱ ነው።

40. እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤ይታደጋቸዋልም፤ከክፉዎች እጅ ነጥቆ ያወጣቸዋል፤እርሱን መጠጊያ አድርገዋልና ያድናቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 37