ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 37:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. እግዚአብሔር የንጹሐንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።

19. በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።

20. ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይሆናሉ፤ይጠፋሉ፤ እንደ ጢስም ተነው ይጠፋሉ።

21. ኀጢአተኛ ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ጻድቅ ግን ይቸራል።

22. እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤እርሱ የሚረግማቸው ግን ይጠፋሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 37