ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 37:11-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

12. ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።

13. እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፤ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።

14. ድኾችንና ችግረኞችን ለመጣል፣አካሄዳቸው ቀና የሆነውንም ለመግደል፣ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ቀስታቸውንም ገተሩ።

15. ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ቀስታቸውም ይሰበራል።

16. የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል።

17. የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፤ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 37