ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 35:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. የሰላም ንግግር ከአፋቸው አይወጣም፤ዳሩ ግን በምድሪቱ በጸጥታ በሚኖሩት ላይ፣ነገር ይሸርባሉ።

21. አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ፤“ዕሠይ! ዕሠይ! በዐይናችን አየነው” አሉ።

22. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል፤ጌታ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።

23. አምላኬ፣ ጌታዬ፤ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ!ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ።

24. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ በጽድቅህ ፍረድልኝ፤በእኔም ላይ ደስ አይበላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 35