ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 35:2-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ፤እኔንም ለመርዳት ተነሥ።

3. በሚያሳድዱኝ ላይ፣ጦርና ጭሬ ምዘዝ፤ነፍሴንም፣“የማድንሽ እኔ ነኝ” በላት።

4. ሕይወቴን የሚፈልጓት፣ይቅለሉ፣ ይዋረዱ፤እኔን ለማጥፋት የሚያሤሩ፣ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

5. በነፋስ ፊት እንዳለ እብቅ ይሁኑ፤ የእግዚአብሔር መልአክ ያሳዳቸው።

6. መንገዳቸው ጨለማና ድጥ ይሁን፤ የእግዚአብሔር መልአክ ያባራቸው።

7. ያለ ምክንያት ወጥመዳቸውን በስውር አስቀምጠውብኛልና፤ያለ ምክንያት ለነፍሴ ጒድጓድ ቈፍረውላታል።

8. ያልታሰበ ጥፋት ይምጣባቸው፤የሰወሩት ወጥመድ ይያዛቸው፤ይጠፉም ዘንድ ወደ ጒድጓዱ ይውደቁ።

9. ነፍሴም በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤በማዳኑም ሐሤት ታደርጋለች።

10. የሠራ አካላቴ እንዲህ ይልሃል፤“እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ማን አለ?ድኻውን ከእርሱ ከሚበረቱ፣ችግረኛውንና ምስኪኑን ከቀማኞች ታድናለህ”።

11. ጨካኝ ምስክሮች ተነሡ፤ስለማላውቀውም ነገር ጠየቁኝ።

12. በበጎ ፈንታ ክፉ መለሱልኝ፤ነፍሴንም ብቸኛ አደረጓት።

13. እኔ ግን እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፤ነፍሴንም በጾም አደከምኋት፤ጸሎቴም መልስ አጥቶ ወደ ጒያዬ ተመለሰ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 35