ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 34:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።

14. ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም።

15. የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው።

16. መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት፣ የእግዚአብሔር ፊት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።

17. ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 34