ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 33:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት።

7. የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።

8. ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።

9. እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤አዞአልና ጸኑም።

10. እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 33