ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 33:12-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. እግዚአብሔር አምላኩ የሆነው ሕዝብ፣ለርስቱ የመረጠውም ወገን የተባረከ ነው።

13. እግዚአብሔር ከሰማይ ይመለከታል፤የሰውንም ልጆች ሁሉ ያያል፤

14. ከማደሪያው ቦታ ሆኖ፣በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ይመለከታል፤

15. እርሱ የሁሉን ልብ የሠራ፣የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያስተውል ነው።

16. ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም።

17. በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤በብርቱ ጒልበቱም ማንንም አያድንም።

18. እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ምሕረቱንም በሚጠባበቁት ላይ አትኵረዋል።

19. በዚህም ነፍሳቸውን ከሞት ያድናል፤በራብ ዘመንም በሕይወት ያኖራቸዋል።

20. ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርጋለች፤እርሱ ረዳታችንና መጠጊያችን ነው።

21. ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋል፤በቅዱስ ስሙ ታምነናልና።

22. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተስፋ ባደረግንህ፣በእኛ ላይ ምሕረትህ ትሁን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 33