ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 33:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል።

2. እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።

3. አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።

4. የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነውና፤የሚሠራውም ሁሉ የታመነ ነው።

5. እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል፤ምድርም በምሕረቱ የተሞላች ናት።

6. በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት።

7. የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።

8. ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።

9. እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤አዞአልና ጸኑም።

10. እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል።

11. የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን ለዘላለም ይጸናል፤የልቡም ሐሳብ ለትውልድ ሁሉ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 33