ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 31:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ከሰዎች ሤራ፣በማደሪያህ ውስጥ ትሸሽጋቸዋለህ፤ከአንደበት ጭቅጭቅም፣በድንኳንህ ውስጥ ትከልላቸዋለህ።

21. በተከበበች ከተማ ውስጥ፣የሚያስደንቅ ምሕረቱን ያሳየኝ፣ እግዚአብሔር ይባረክ።

22. እኔ በደነገጥሁ ጊዜ፣“ከዐይንህ ፊት ተወግጃለሁ” አልሁ፤አንተ ግን ወደ አንተ ስጮኽ፣የልመናዬን ቃል ሰማህ።

23. እናንተ ቅዱሳኑ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ውደዱት! እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል፤ትዕቢተኞችን ግን ፈጽሞ ይበቀላቸዋል።

24. እግዚአብሔርን ተስፋ የምታደርጉ ሁሉ፤በርቱ፤ ልባችሁም ይጽና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 31