ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 31:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ተተግኛለሁ፤እንግዲህ ዕፍረት ከቶ አይድረስብኝ፤በጽድቅህም ታደገኝ።

2. ጆሮህን ወደ እኔ መልሰህ ስማኝ፤ፈጥነህ አድነኝ፤መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ታድነኝም ዘንድ ምሽግ ሁነኝ።

3. አንተ ዐለቴና መጠጊያዬ ነህና፣ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤መንገዱንም ጠቍመኝ።

4. አንተ መጠጊያዬ ነህና፣በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ።

5. መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤አንተ ተቤዠኝ።

6. ለከንቱ ጣዖታት ስፍራ የሚሰጡትን ጠላሁ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።

7. በምሕረትህ ደስ እሰኛለሁ፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤መከራዬን አይተሃልና፤የነፍሴንም ጭንቀት ዐውቀሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 31