ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 29:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤ የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።

9. የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤ጫካዎችንም ይመነጥራል፤ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።

10. እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጦአል፤ እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።

11. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 29