ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 27:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ማንን እፈራለሁ?

2. ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።

3. ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ልቤ አይፈራም፤ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ልበ ሙሉ ነኝ።

4. እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤እርሷንም እሻለሁ፤ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 27