ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 26:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤ከዐመፀኞችም ጋር አልቀመጥም።

6. እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤

7. የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣ታምራትህንም አወራ ዘንድ ነው።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ የምትኖርበትን ቤት፣የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።

9. ነፍሴን ከኀጢአተኞች ጋር፣ሕይወቴንም ከደም አፍሳሾች ጋር አታስወግዳት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 26