ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 21:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በምትገለጥበት ጊዜ፣እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች።

10. ዘራቸውን ከምድር፣ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ።

11. ክፋት ቢያስቡብህ፣ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤

12. በመጡበት ትመልሳቸዋለህና፤ቀስትህንም በፊታቸው ላይ ታነጣጥራለህ።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ በብርታትህ ከፍ ከፍ በል፤ኀይልህን እናወድሳለን፤ እንዘምራለንም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 21