ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 21:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው።

6. ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍስሓም ደስ አሰኘኸው፤

7. ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፤ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ከቆመበት አይናወጥም።

8. እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ፈልጋ ትይዛለች።

9. በምትገለጥበት ጊዜ፣እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 21