ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 21:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ሕይወትን ለመነህ፤ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።

5. ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው።

6. ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍስሓም ደስ አሰኘኸው፤

7. ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፤ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ከቆመበት አይናወጥም።

8. እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ፈልጋ ትይዛለች።

9. በምትገለጥበት ጊዜ፣እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች።

10. ዘራቸውን ከምድር፣ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ።

11. ክፋት ቢያስቡብህ፣ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤

12. በመጡበት ትመልሳቸዋለህና፤ቀስትህንም በፊታቸው ላይ ታነጣጥራለህ።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ በብርታትህ ከፍ ከፍ በል፤ኀይልህን እናወድሳለን፤ እንዘምራለንም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 21