ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 21:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥ በኀይልህ ደስ ይለዋል፤በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል።

2. የልቡን መሻት ሰጠኸው፤የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም። ሴላ

3. መልካም በረከት ይዘህ በመንገዱ ላይ ጠብቀኸው፤የንጹሕ ወርቅ ዘውድም በራሱ ላይ ደፋህለት።

4. ሕይወትን ለመነህ፤ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።

5. ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው።

6. ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍስሓም ደስ አሰኘኸው፤

7. ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፤ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ከቆመበት አይናወጥም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 21