ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 20:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የልብህን መሻት ይስጥህ፤ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።

5. በአንተ ድል ደስ ይበለን፤በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ።

6. እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድንአሁን ዐወቅሁ፤የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።

7. እነዚህ በሰረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤እኛ ግን ትምክህታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።

8. እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤እኛ ግን ተነሣን፤ ጸንተንም ቆምን።

9. እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥን አድን፤እኛም በጠራንህ ቀን ስማን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 20