ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 17:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅንነት የቀረበውን አቤቱታዬን ስማ፤ጩኸቴንም አድምጥ፤ከአታላይ ከንፈር ያልወጣውን፣ጸሎቴን አድምጥ።

2. ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ዐይኖችህም ፍትሕን ይዩ።

3. ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋብለህ ፈተንኸኝ፤ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም።

4. ከሰዎች ተግባር፣በከንፈርህ ቃል፣ከዐመፀኞች መንገድ፣ራሴን ጠብቄአለሁ።

5. አረማመዴ በመንገድህ ጸንቶአል፤እግሮቼም አልተንሸራተቱም።

6. አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 17