ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 16:3-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በምድር ያሉ ቅዱሳን፣ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።

4. ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ሐዘናቸው ይበዛል፤እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስም፤ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤

5. እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ዕጣዬም በእጅህ ናት።

6. መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።

7. የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።

8. እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።

9. ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤

10. በሲኦል ውስጥ አትተወኝምና፤ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።

11. የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 16