ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 16:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣በከለላህ ሰውረኝ።

2. እግዚአብሔርን፣ ‘አንተ ጌታዬ ነህ፤ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም”አልሁት።

3. በምድር ያሉ ቅዱሳን፣ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።

4. ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ሐዘናቸው ይበዛል፤እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስም፤ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፤

5. እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ዕጣዬም በእጅህ ናት።

6. መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 16