ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 149:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።

5. ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።

6. የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣ባለ ሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤

7. በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤ሰዎችንም ይቀጣሉ፤

8. ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤

9. ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው።ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 149